ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ህዳር 21/2013 (ኢዜአ) ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የህግ የበላይነት በማስከበር ሂደት ላይ ድል ለተጎናፀፈው የአገር መከላክያ ሰራዊት የ7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍና የደም ልገሳ አደረገ፡፡

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢተው ደመላሽ እንዳሉት ሰራተኞች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለሰራዊቱ ድጋፍ ለማድረግ በገቡት ቃል መሰረት 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር አበረክቷል። ሰራተኞቹ የገንዘብ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ የደም ልገሳ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል። በቀጣይም ለሰራዊቱ ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ የድርጅቱ ሰራተኞች ዝግጁ መሆናቸውን ስራ አስኪያጁ አረጋግጠዋል። ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በቀረበ ጥሪ መሰረት የጤና ባለሙያዎች ለሰራዊቱ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ሲወስኑ ሸገር ነፃ የትራነስፖርት አገልግሎት መስጠቱን አንስተዋል፡፡ ከፀጥታ ጋር ተያዞም ትራንስፖርት አንዱ የስጋት ቦታ በመሆኑ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የቁጥጥርና ክትትል ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት 2 ሺህ 684 ሰራተኞች እንዳሉት መረጃዎች ይጠቁማሉ።

0 0 vote
Article Rating

You may also like...

Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x