በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 510 ኩንታል ስኳር ለሸማቾች ሊከፋፈል ነው

የሸዋ ሮቢት ከተማ ኮሚኒኬሽን

ከሰሞኑን ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ሲዘዋወር በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር የዋለ 510 ኩንታል ስኳር ከዛሬ ጀምሮ ለሸማች ማህበረሰቡ እንደሚከፋፈል የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳዳር ገልጿል።

እንደ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ገለጻ ከሆነ ከቀናት በፊት 2 የጭነት ተሸከርካሪዎች ምንም አይነት ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በህገ ወጥ መንገድ 510 ኩንታል ስኳር ይዘው ሲንቀሳቀሱ በከተማው የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የከተማው የህገወጥ ተከላካይ ግብረ ኃይል ለፍርድ ቤት በሚያቀርበው መረጃ መሰረት ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ግብር ኃይሉ ስኳሩ ለሸማች ማህበረሰብ ተሸጦ ገንዘቡ በአደራ መልክ እንዲቀመጥ ውሳኔ አሳልፏል።

ስኳሩ ለሸማችና ለቸርቻሪዎች የተሰራጨ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ማህበረሰቡ ኩፖኑን በመያዝ በተመደበት ሱቅ እና ሸማች ማህበር በመሄድ ስኳሩን መወሰድ የሚችል መሆኑን ጽ/ቤቱ አስታውቋል።

0 0 vote
Article Rating

You may also like...

Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x