በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች መንግስት በከሀዲው የህወሓት ቡድን በመውሰድ ላይ ያለውን ህግ የማስከበርና የህልውና ዘመቻ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የአዳማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ በሰላማዊ ሰልፍ ገልጸዋል፡፡
ከአዳማ በተጨማሪም የሞጆ፣ የምዕራብ ሃረርጌ፣ የሱሉልታ፣ የቦረና ዞን እና የቡራዩ ከተማ ነዎሪዎችም ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ድጋፋቸውን አሳይተዋል፡፡
እንዲሁም በዱከም፣ ለገጣፎ፣ ሰበታ፣ ሆለታ ከተሞችም ቡድኑን የሚያወግዙ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡
በሰልፉ ስግብግቡ የትህነግ ቡድን ጥፋት ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ታሪክና ስነልቦና የማይገጥም መሆኑን እና ቡድኑ ሀገር ለማፍረስ የሚሰራውን ሴራ በጋራ እንደሚያከሽፉ ሰልፈኞቹ ተናግረዋል።
መንግስት በመስራት ላይ ያለውን የህግ ማስከበር ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል የተጠየቀ ሲሆን በሚጠበቅባቸው ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም ገልፀዋል።
@Fbc