በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልኡክ በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን አቃቂ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኙ

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልኡክ በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን አቃቂ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልኡክ በኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን አቃቂ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኙ። የስንዴ ማሳውን የጎበኙት አቶ ሽመልስ በወረዳው የኢለቹ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋርም ባሉ ችግሮች ዙሪያ መምከራቸውን ከኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነ መረጃ ያመለክታል። በዚሁ ወቅትም በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮችን ኑሮ ለማሻሻል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ሽመልስ ገልፀዋል። የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞንአስተዳዳሪ አቶ ግርማ ሀይሉ፥ እንደ ኦሮሚያ ክልል ዘንድሮ በመስኖ ከማልማት ከታቀደው 300 ሺህ ሄክታር ስንዴ ውስጥ 17 ሺህ ሄክታር በዞኑ እየለማ መሆኑን አስታውቀዋል።

0 0 vote
Article Rating

You may also like...

Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x