በኢትዮጵያ እና በሌሎች የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊጥል እንደሚችል የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት የልህቀት ማዕከል አስጠነቀቀ፡፡

Amharic news - Ethiopian map

በኢትዮጵያ እና በሌሎች የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊጥል እንደሚችል የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት የልህቀት ማዕከል አስጠነቀቀ፡፡

ማዕከሉ በተለይም በመካከለኛው እና ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊጥል ይችላል ብሏል። በእነዚህ ሀገራት የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋዎችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ የልህቀት ማዕከሉ አስጠንቅቋል፡፡ የዝናብ ትንበያው ከዛሬ ጀምሮ በሚቀጠሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የሚጠበቅ ሲሆን በምዕራብ እና መካከለኛው ኢትዮጵያ ጥቂት ቦታዎች ከ 200 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ ዝናብ ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እንዲሁም በጎረቤት ሀገራት ደቡብ-ምዕራብ ሱዳን ፣ ከሰሜን-ምዕራብ እስከ ደቡብ-ምዕራብ ደቡብ ሱዳን፣ በምዕራብ እና፣ ሰሜን-ምስራቅ ሶማሊያ እንዲሁም በሰሜን-ምዕራብ ዩጋንዳ እና ምዕራብ ኬንያ ከ 50 እስከ 200 ሚሊ ሜትር የሆነ መካከለኛ ዝናብ ይኖራል፡፡ በሰሜን ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ፣ በማዕከላዊ ሱዳን ፣ በሰሜን ምዕራብ ኤርትራ ፣ በምዕራብ እና ማዕከላዊ ደቡብ ሱዳን፣ በሰሜን እና በደቡብ ሶማሊያ ፣ በጅቡቲ የባህር ዳርቻዎች ፣ በማዕከላዊ እና በምስራቅ ዩጋንዳ አንዳንድ አካባቢዎች ከ50 ሚሊ ሜትር በታች የሆነ ቀላል ዝናብ ይኖራል ተብሏል፡፡

0 0 vote
Article Rating

You may also like...

Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x