አለም አቀፉ የፅዳት ቀን በአዲስ አበባ በፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አለም አቀፉ የፅዳት ቀን በአዲስ አበባ በፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ እየተከበረ ነው።ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ በመንግስት ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች እና በሀይማኖት ተቋማት የፅዳት መርሃግብር እየተካሄደ ነው።የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በርካታ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች በየአካባቢያቸው በንቅናቄው እየተሳተፉ ይገኛሉ። ወይዘሮ አዳነች በዛሬው እለት ከ1 ሚልዮን በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የአለም ማህበረሰብን በመቀላቀል አካባቢያቸውንና ከተማቸውን እያፀዱ መሆኑን ተናግረዋል። በዛሬው እለት ትምህርት ቤቶችን የማጽዳት እና የጸረ ተሕዋሲያን ኬሚካል ርጭት ስራ መካሄዱንም ነው ያመለከቱት። “ባሳለፍነው ዓመት ታትረው የጽዳት ስራ ሲሰሩ የነበሩ ነዋሪዎቻችንን እያመሰገንኩ ከዛሬ ጀምሮ ሁላችንም በመተባበር እና በአንድነት መንፈስ አዲስ አበባ ስሟን እና ክብሯን የሚመጥን ጽዳት እንዲኖራት በእንዲህ ቀን ዘመቻ ሳይሆን ሁሌም በማጽዳት ለነዋሪዎቿ ምቹ ለቱሪዝም ሳቢ ከተማ እድናደርጋት ጥሪዬን አቀርባለው” ብለዋል በመልዕክታቸው። በዛሬው ፅዳትን በመጠበቅ የተሻለ አፈፃፅም ያላቸው አካባቢዎች እውቅና እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል።

0 0 vote
Article Rating

You may also like...

Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x