አንጋፋው የፖለቲካ ተንታኝ ፕሮፌሰር አል ማሪያም ‹‹በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ ለምትፈልጉ ሁሉ!›› በሚል ርእስ በእንግሊዘኛ ባቀረቡት አስተያየት ‹‹ከአሸባሪ ጋር ትደራደራላችሁ ወይ?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

አንጋፋው የፖለቲካ ተንታኝ ፕሮፌሰር አል ማሪያም ‹‹በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ ለምትፈልጉ ሁሉ!›› በሚል ርእስ በእንግሊዘኛ ባቀረቡት አስተያየት ‹‹ከአሸባሪ ጋር ትደራደራላችሁ ወይ?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

አንጋፋው የፖለቲካ ተንታኝ ፕሮፌሰር አል ማሪያም በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ ለምትፈልጉ ሁሉ በሚል ርእስ በእንግሊዘኛ ባቀረቡት አስተያየት ‹‹ከአሸባሪ ጋር ትደራደራላችሁ ወይ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ 

አልማሪያም በዚህ አስተያየታቸው ‹‹አለም አቀፍ ጣል ገቦች አንድ ማወቅ ያለባችሁ ነገር ለኢትዮጵያ ችግር መፍትሄ የሚገኘው ከኢትዮጵያ ነው፣ ለአፍሪካ ችግርም መፍትሄው የአፍሪካ ነው፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሀት ጋር እንዲደራደር ጫና ለማድረግ የሚፈልጉ ጣልቃ መግባታቸውን አቁመው ራሳቸውን አንድ አጭር ጥያቄ ይጠይቁ፡፡ እነሱ በብሄራዊ መከላከያ ሰራዊታቸው ላይ ጦርነት ካወጀ፣ ቁጥራቸው የበዛ ህዝባቸውን ከገደለ፣ ህገ መንግስታቸውን ካላከበረና በአሸባሪነት ከተመዘገበ ድርጅት ጋር ይደራደራሉ? አያደርጉትም›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም አብይ አህመድ አሁን እንዲደራደሩ ጫና እየተደረገባቸው ያለው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ህወሀት) ከተባለ በአሸባሪነት ከተመዘገበ ድርጅት ጋር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ህወሀት ‹‹ግሎባል ቴረሪዝም ዳታ ቤዝ›› በተሰኘ የአሸባሪዎች መዝገብ ላይ መስፈሩንም ጠቅሰዋል፡፡ አስተያየታቸውን ሲቀጥሉም ‹‹እዚህ ላይ ስህተት ውስጥ መግባት የለብንም፡፡ በምንም መልኩ በቅርፁም ሆነ በአይነቱ የብሄር ግጭት የለም፡፡ በፌዴራል መንግስቱ እየተወሰደ ያለው እርምጃ በህወሀት ላይ እንጂ በትግራይ ህዝብ ላይ አይደለም፡፡ የትግራይ ህዝብ በህወሀት ወንጀሎች በከፍተኛ ደረጃ የተጎዳ ነው፡፡ በህዝቡ ስም በርካታ ወንጀሎችንና ከፍተኛ ሙስና ፈፅሟል፡፡ ህወሀት የትግራይ ህዝብን የፖለቲካ ከለላ አድርጎ እንደተጠቀመበት ሁሉ አሁን ወታደራዊ እርምጃ ሲወሰድበት በከለላነት እየተጠቀመበት ይገኛል›› ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ ባለፈው ሳምንት የህወሀት አሸባሪዎች በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ፈፅመው ጦርነት ማወጃቸው እየታወቀ አሁን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ላይ ከእነዚህ አሸባሪዎች ጋር እንዲደራደሩ ጫና እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ከአሸባሪ ጋር የትኛውም አገር ከቶም ሊደራደር እንደማይችልም ገልፀዋል፡፡ ይህንን አባባላቸውን ሲያስረዱም ‹‹የአሜሪካ መንግስት ህገ መንግስቱንና ጦር ሰራዊቱን መስዋእት አድርጎ እንዲሁም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ጥሎ ከአሸባሪዎች ጋር ፈፅሞ አይደራደርም፡፡ የእንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ጀርመን፣ ፖላንድና ሩሲያ መንግስታትም ፈፅሞ አያደርጉትም፡፡ የናይጄሪያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ መንግስታትም ከአሸባሪ ጋር አይደራደሩም፡፡ ከአሸባሪ ጋር መደራደር ሌሎች አሸባሪዎችን መጥራት ነው፡፡›› ሲሉ አስታውቀዋል።

0 0 vote
Article Rating

You may also like...

Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x