የህወሓትን የጥፋት ተልዕኮ የሚያስፈፅሙ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሓትን የጥፋት ተልዕኮ የሚያስፈፅሙ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን ለመደምሰስ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጋር እየተሰራ እንዳለ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡

ፓርቲው የፀረ-ሰላም ቡድኑ በገንዘብና በቁስሳቁስ ተደልሎ ለጥፋ የሚንቀሳቀስ፣ አላማ ቢስ መሆኑን አሳውቋል፡፡ ፓርቲዎ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳታወቀው ቡድኑን ለመደምሰስ የመከላከያ ሰራዊት፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ኃይልና ህዝቡ በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ንፁሃን ዜጎች የሰላም አየር እንዲተነፍሱ ለማድረግ ፓርቲው ከሚመለከተው አካል ጋር በጥምረት እየሰራ እንዳለ አሳውቋል፡፡ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ፀረ-ሰላም የህወሓት ቅጥረኞች በንፁሃን ዜጎቻችን ላይ ዘግናኝ ጥቃት መፈፀማቸውን አስታውሶ፣ የህግ የበላይነትን ለማስከበር የእኩይ ድርጊቱ ፈፃሚዎችና እጃቸው ያሉባቸው አካላት ላይ በሰላም አስከባሪ ኃይሉ እየተወሰደ ያለው ተመጣጣኝ እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አሳውቋል፡፡ የስግብግቡ የህወሓት ጁንታ ቡድን አጀንዳ ተቀባዮች እና ተላላኪዎች በመተከል ዞን ከወንበራ ወደ ግልገል በለስ በህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ በመጓዝ ላይ በነበሩ ንፁሃን ዜጎቻች ላይ በድባጢ ወረዳ ዘግናኝ የሆነ ጥቃት በመፈፀም ከ30 በላይ ሰላማዊ ዜጎቻች ህይወት ማለፉን ጽ/ቤቱ አስታውሷል፡፡


ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን ሲመታ በሳንባው የሚተነፍሱ ሽፍቶችና ጀሌዎች የሚገቡበትን መቀመጫ ሲጠፋቸው ተስፋ በመቁረጥ እንደ እብድ ውሻ ሁሉንም ዜጎቻችንን በየቦታው እየተነኮሱ ይገኛሉ ብሏል ፓርቲው፡፡ እስካሁን በተደረገ የህግ የበላይነት የማስከበር ስራ በኮማንድ ፖስቱ በተወሰደ እርምጃ 20 የፀረ-ሰላም ኃይሎች መደምሰሳቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ ቢሮ ያረጋገጠ ሲሆን፤ አካባቢውን ለማረጋጋት እየተወሰደ ያለው ፍትሃዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው በመግለጫው ያነሳው፡፡

0 0 vote
Article Rating

You may also like...

Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x