የትህነግ ቡድን በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ የፈፀመው ክህደት እና ጥቃት መላው ዕዛችንን አስቆጥቷል-ምእራብ ዕዝ

የትህነግ ቡድን በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ የፈፀመው ክህደት እና ጥቃት መላው ዕዛችንን አስቆጥቷል-ምእራብ ዕዝ. አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ). የእናት ጡት ነካሹ የትህነግ ቡድን በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ የፈፀመው ክህደት እና ጥቃት መላው ዕዛችንን አስቆጥቷል ሲል የምዕራብ ዕዝ ገልጿል። የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ተወካይ ኮሎኔል ቢረሳው ሽፈራው÷ የእናት ጡት ነካሹ የትህነግ ቡድን በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ የፈፀመው ክህደት እና ጥቃት እንደተሰማ መላው የምዕራብ ዕዝ የሠራዊት አባላትን በእጅጉ አስቆጥቷል ብለዋል፡፡ የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በሪሶ ተመስገን በበኩላቸው÷ በሠራዊቱ ላይ የተፈፀመው ክህደት እና ጥቃት ለባዕድ ሃገር አሳልፎ ከመስጠት በላይ ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ከሀዲው የህወሓት ቡድን ተደምስሶ ለፍርድ እስከሚቀርብ ድረስ የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር እና ነዋሪዎች ከጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ጋር በጋራ እንደሚቆሙም ተናግረዋል ፡፡ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባል ዋና ሳጅን ዳዊት ሃይሉ ደግሞ ሠራዊቱ ምስጋና እና ክብር ሲገባው ጥቃት ተፈፅሞበታል ነው ያሉት ፡፡ ይህ ስግብግብ ጁንታ ቡድን ተይዞ ህግ እስከሚቀርብ ድረስ ከጀግናው ሠራዊት ጎን እንሰለፋለን ሲሉ መናገራቸውን ከኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ @Fbc

0 0 vote
Article Rating

You may also like...

Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x