የጉራጌ ዞንና የኮንታ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት 373 ሰንጋዎችና 17 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21/2013 (ኢዜአ) የደቡብ ክልል ጉራጌ ዞንና ኮንታ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሠራዊት 373 ሰንጋዎችና 17 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከቱ።

የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችም 810 ኩንታል ስኳር ለግሰዋል። የጉራጌ ዞን ሕዝብ 223 ሰንጋዎችና 15 ሚሊዮን ብር፣ የኮንታ ልዩ ወረዳም150 ሰንጋዎችና 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ሰጥተዋል። የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችም ግምቱ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ 810 ኩንታል ስኳር አበርክቷል። ድጋፉ የህወሓት አጥፊ ቡድን በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ በፈፀመው ጥቃት የተቆጣው ሕዝብ አጋርነቱን ለማሳየት ያደረገው መሆኑ ተነግሯል። የሕግ ማስከበርና የሕልውና ዘመቻው እስከሚጠናቀቅ የሕዝቡ ድጋፉ እንደማይቋረጥም ተገልጿል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሐመድ ጀማል የጉራጌ ማኅበረሰብ በአገር ላይ ለሚቃጣ ጥቃት የትኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። በትግራይ ክልል በአጥፊው ቡድን የወደሙ የመሰረተ ልማት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል። የኮንታ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፈንታሁን በለጠም ሕዝቡ ከገንዘብና ከዓይነት አስተዋጽኦ በላይ ለማድረግ ዝግጁ ነው ብለዋል። ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ ሕዝቡ ለመከላከያ ሠራዊት እያደረገው ያለው ድጋፍ መቀጠሉን ገልጸዋል። የሕዝቡ ድጋፍ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለውን የአገር ፍቅር ያየንበት ነውም ብለዋል።

0 0 vote
Article Rating

You may also like...

Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x