ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ነባሮቹን የ10 ፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ነባሮቹን የ10 ፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።  ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ የሁለት መቶ ብር ኖትን ወደ ሥራ ታስገባለች። የ5 ብር ገንዘብ ባለበት ቀጥሎ፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ሣንቲም የሚለወጥ ይሆናል። የብር ኖቶቹን ለምን መቀየር አስፈለገ ?.  መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንዲሁም ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ የሚዘዋወረውን ገንዘብ ለመሰብሰብ ፣  ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ፣   ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ ለማስቀረት ፣  እርምጃው የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ እጥረትን ለመቋቋም እንዲችሉም እንደሚያግዝ ከPMO ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አሁን በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ?. አብዛኛው የሕትመት ሥራ ተገባዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግምጃ ቤት ይገኛል። የስርጭት ስርዓት እና ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን ፣ በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት ይተገበራል። በገንዘብ ቅያሬው ሂደት ውስጥ የጸጥታ አስከባሪ አካላት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን ፣ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ከማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ያስፈጽማሉ ተብሏል። ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ ፣ ሂደቱን በበላይነት ያስተባብራል።  የክልል መንግሥታትም ተመሳሳይ ኮማንድ ፖስት አቋቁመው ሥራውን እንዲያከናውኑ ይጠበቃል።

0 0 vote
Article Rating

You may also like...

Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments
0
Would love your thoughts, please comment.x
()
x